የዶክተር ያለህ የተዋወቅነው ከስድስት ወራት በፊት በፌስቡክ ነው። የሚኖረው ከኢትዮጵያ ውጭ ነው። በጣም ተዋደን ፍቅረኛሞች ሆንን። ወደ አዲስ አበባ መጥቶ ቀለበት እንደምናደርግ ቃል ገባልኝ። በየሰዓቱ እንደዋወላለን፤ እንፃፃፋለን። ብዙ ፎቶዎችንም እንላላካለን። በመሃል ግን እርቃኔን ፎቶ ተነስቼ እንድልክለት ጠይቆኝ እምቢ አልኩት፡፡ "አታምኚኝም ማለት ነው፤ እጮኛሽ አይደለሁም እንዴ" ብሎ በጣም ከወቀሰኝ በኋላ ጥፋተኝነት ተሰምቶኝ ላኩለት። ነገር ግን ሰሞኑን ባህሪው ተቀይሮብኝ ስልክ መደወል አቆመ። ለምን ትጠፋለህ ብዬ ስጠይቀው "አትጨቅጭቂኝ፤ ማቆም እንችላለን" አለኝ። ይባስ ብሎ "ከእኔ ጋር አቁመሽ ሌላ ፍቅረኛ ብትይዢ ያንን ፎቶሽን ፌስቡክ ላይ እለቀዋለሁ" ብሎ አስፈራራኝ። በጣም ደነገጥኩ። ያለው አሜሪካ እንደመሆኑ እንዴት እንደማስቆመው አላውቅም። ጭንቀት ውስጥ ወድቄያለሁ። ስህተት እንደሠራሁ አውቃለሁ፤ ግን ምን እንደማደርግ ጨንቆኛል። መፍትሄ ስጡኝ? ኤስ ነኝ ከአ/አ
- Category
- Misc