ዶናልድ ትራምፕ ሻወር ቤት ውሃ ቀነሰብኝ ብለው አማረሩ

  • 77

ዶናልድ ትራምፕ ሻወር ቤት ውሃ ቀነሰብኝ ብለው አማረሩ

ፕሬዝዳንት ትራምፕ

የአሜሪካ መንግሥት የገላ መታጠብያ ቧንቧ ጭንቅላት ምን ያህል ውሃ ማፍሰስ አለበት የሚለውን ደንብ ለመቀየር እያጤነ ነው፡፡

ይህን ደንብ ለማጤን የተገደደው ደግሞ ከሕዝብ በመጣ ቅሬታ ሳይሆን በዶናልድ ትራምፕ ጸጉር የተነሳ ነው፡፡

የ1992 የአሜሪካ በተደነገገ ሕግ የአሜሪካ የሻወር ቧንቧዎች ጭንቅላት በደቂቃ ከ2.5 ጋሎን በላይ እንዳያፈስ ያስገድዳል፡፡

ይህም ብክነትን ለመከላከል የወጣ ደንብ ነው፡፡

የትራምፕ አስተዳደር ይህንን መጠን ለመጨመር ይሻል፡፡ ምክንያቱም ትራምፕ ገላዬን ስታጠብ በቂ ውሃ እየፈሰሰልኝ አይደለም ሲሉ ቅሬታ በማቅረባቸው ነው፡፡

የሸማቾች ማኅበር እና የአካባቢ ጥበቃ ተቆርቋሪዎች የሻወር ውሃ ግፊትን ከዚህ በላይ መጨመር አላስፈላጊነ ከመሆኑም በላይ ለብክነት ይዳርጋል ብለዋል፡፡

ይህ የሻወር ቧንቧ ውሀ ደንብ ሊቀየር የታሰበው የአሜሪካ የፍሳሽ ኃይል ባለሥልጣን ባለፈው ወር በዶናልድ ትራምፕ የቀረበውን ቅሬታ ተንተርሶ ነው፡፡

‹‹እነዚህ የሻወር ውሃ ማፍሰሻዎች ግን…›› አሉ ትራምፕ ከሳምንታት በፊት፣ ‹‹…ለመሆኑ ውሃ በበቂ ይፈስላችኋል? ለኔ ግን ውሃ አይወርድልኝም፡፡ ልብስ አውልቃችሁ ሻወር ቤት ገብታችሁ ትቆማላችሁ፣ ለረዥም ሰዓት ውሀው ግን ግፊት የለውም፡፡ ስለናንት ባላውቅም እኔ ግን በተለይ ፀጉሬ እስትክክል ብሎ እንዲታጠብ እፈልጋለሁ፡፡ ››

የአሜሪካ የኃይል ጥበቃና የቁሳቁሶች ደረጃ መዳቢ ቡድን ኃላፊ አንድሩ ዴላስኪ ‹‹ ትራምፕ ያቀረቡት ሀሳብ ‹የጅል ሐሳብ›› ብለውታል፡፡

በያንዳንዱ የሻወር ቧንቧ ቀዳዳ 2.5 ጋሎን ውሀ ይፍሰስ ማለት በጠቅላላው በደቂቃ ከ10 እስከ 15 ጋሎን ማለት ነው፡፡ ይህ የውሃ ግፊት ሻወር የሚወስደውን ሰውዬ ከሻወር ቤት ጠርጎ ሊያስወጣው ሁሉ ይችላል ብለዋል ለአሶሺየትድ ፕሬስ

በትራምፕ ምክንያት የሚቀየረው ደንብ ወደ ፍርድ ቤት ሊሄድ ይችላል ብሏል ሮይተርስ፡፡

ዶናልድ ትራምፕ ጸጉራቸው ሰው ሰራሽ ነው ወይስ የተፈጥሮ የሚለው አሁንም የመገናኛ ብዙኃንት መነጋገርያ ነው፡፡• ተጨማሪ ትኩስ ዜናዎች