ኮሮናቫይረስ፡ በስፔን አንድ ግዛት ሕዝብ በሚሰበሰብበት ስፍራ ሲጃራ ማጤስ ታገደ

  • 42

ኮሮናቫይረስ፡ በስፔን አንድ ግዛት ሕዝብ በሚሰበሰብበት ስፍራ ሲጃራ ማጤስ ታገደ

በመንገድ ላይ የምታጤስ ሴት

ጋሊሲያ የተሰኘችው የስፔን አንድ ክልል ህዝብ በተሰበሰበበት ስፍራ ሲጃራ ማጤስን የኮቪድ-19 ስርጭትን ያስፋፋል በሚል አገደች።

በክልሉ በጎዳናዎች ላይም ሆነ ሕዝብ በሚሰበሰብባቸው ስፍራዎች ሙሉ በሙሉ እገዳው የተጣለ ሲሆን በዚህም የተነሳ አካላዊ ርቀት መጠበቅ በማይቻልባቸው እንደ በምግብ ቤቶች፣ መጠጥ ቤቶች ባሉ ስፍራዎች ክልከላው ተቀምጧል።

በስፔን በምዕራብ ሰሜን የምትገኘው ይህቺ ክልል ምንም እንኳ ሌሎች ይከተሏታል ተብሎ ቢታሰብም እንዲህ አይነት ገደብን ስታስቀምጥ ግን የመጀመሪያዋ ናት።

ውሳኔው የመጣው ስፔን በምዕራብ አውሮጳ ከሚገኙ አገራት መካከል ወርሽኙ በፍጥነት ዳግም እየተስፋፋባት ባለበት ሰዓት ነው።

በሰኔ ወር በየዕለቱ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በቀን 150 የነበረ ሲሆን በነሐሴ ግን ወደ 1500 ከፍ ብሏል።

ረብዑ እለት በአንድ ቀን 1690 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተመዘገበ ሲሆን፣ ይህም በመላው አገሪቱ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 330,000 አድርሶታል።

የጋሊሲያ የማጤስ ክልከላ ይፋ የሆነው ባለሙያዎች ለክልላዊ መንግሥት እንደ መከላከያ መንገድ ሃሳባቸውን ካቀረቡ በኋላ ነው።

ውሳኔው በጤና ሚኒስተር የምርምር ቡድን ድጋፍ ያገኘ ሲሆን በማጤስና በኮሮናቫይረስ ስርጭት መስፋፋት መካከል ያለውን ግንኙነት አብራርተዋል።

ባለሙያዎቹ እንዳሉት አጢያሾች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ አለማድረጋቸው የበለጠ ለቫይረሱ እያጋለጣቸው ነው።

እንዲሁም ሰዎች በሚያጤሱበት ወቅት ከአፍንጫቸው የሚወጣ ነጠብጣብ መኖሩን ከዚያም ሲጋራውን ወደ አፋቸው ከመውሰዳቸው በፊት በእጃቸው የሚነኩት መሆኑንም ገልፀዋል።

" በየትኛውም አካባቢ ሲጋራ ማጤስ. . .ሰዎች በአቅራቢያ ካሉ እንዲሁም የአካላዊ ርቀት በሌለበት ከፍተኛ አደጋ ይደቅናል" ያሉት የክልሉ ፕሬዝዳንት አልቤርቶ ኑዋኔዝ ፌይጆ ናቸው።

መንግሥትን የሚያማክረው ቡድን አባል የሆኑት አልቤርቶ ፈርናንዴዝ ቪላር "ይህ በአጢያሶች ዘንድ ድጋፍ የማያገኝ ውሳኔ መሆኑን እናውቃለን" ሲሉ አክለዋል። እንዲሁም " እንደማነምነው በተለየ ሁናቴ ውስጥ ነው ያለነው" ሲሉ የውሳኔውን አስፈላጊነት አጽንኦት ሰጥተውታል።

በደቡብ አፍሪካ ከኮሮናቫይረስ ስርጭት ጋር በተያያዘ ከመጋቢት ወር መጨረሻ ጀምሮ አልኮል መጠጥና ሲጋራ መሸጥ መታገዱ ይታወሳል።

ክልከላው ከጤና ደህንነት ጋር በተያያዘ የቀረበ ሲሆን በባለሙያዎችና በዓለም ጤና ድርጅት ምክር መፈፀሙን አገራቱ ተናግረዋል።

በዩናይትድ ኪንግደም የተሰራ የዳሰሳ ጥናት እንደሚያሳየው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ከተከሰተ ወዲህ ከአንድ ሚሊዮን ሰዎች በላይ ማጤስ በቃኝ ብለዋል። የዩናይትድ ኪንግደም መንግሥት አጢያሾች ከሌሎች በበለጠ ለኮቪድ-19 ምልክቶች ተጋላጭ መሆናቸውን በማንሳት ዜጎቹን ይመክራል።• ተጨማሪ ትኩስ ዜናዎች