ኮሮናቫይረስ፡ ፕሬዝዳንት ትራምፕ የመኪና አምራቹን የመተንፈሻ መሳሪያ እንዲያመርት አዘዙ

  • 28 ማርች 2020
  • 297
ፕሬዝዳነት ትራምፕImage copyright Reuters

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የተሽከርካሪዎች አምራች የሆነው የጄነራል ሞተርስ ለኮሮናቫይረስ ታማሚዎች የሚያገለግል የመተንፈሻ መሳሪያ እንዲያመርት አዘዙ።

ፕሬዝዳንቱ መኪናዎችንና የመኪኖችን አካላት በማምረት በአሜሪካ ትልቁና በዓለም ከታላላቆቹ አንዱ የሆነውን የጄነራል ሞተርስ ዋና ሥራ አስፈጻሚን በትችት ከሸነቆጡ በኋላ ነበር ኩባንያው አሜሪካ በአሁኑ ወቅት የሚያስፈልጋትን እንዲያመርት ያዘዙት።

ተቋማት ለአገር መከላከያ የሚያስፈልጉ ምርቶችን እንዲያመርቱ ፕሬዝዳንቱ ማስገደድ እንደሚችሉ በኮሪያ ጦርነት ጊዜ ለመከላከያ አገልግሎት የሚውሉ ምርቶችን በተመለከተ የወጣውን ደንብ ጠቅሰው ነው ትራምፕ ይህንን ትዕዛዝ ያስተላለፉት።

ፕሬዝዳንቱ መኪና አምራች ኩባንያን በተመለከተ "ጄነራል ሞተርስ ጊዜ እያባከነ ነው" በማለት በዚህ ጊዜ ከኮሮናቫይረስ የአሜሪካዊያንን ህይወት ለመታደግ እርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል ብለዋል።

የህክምና ባለሙያዎቻቸውን ለመከላከል የሚተጉት ቱኒዚያውያን

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ተጨማሪ 15 ቢሊየን ብር ለባንኮች ሊሰጥ ነው

በአሁኑ ጊዜ አሜሪካ ከ104 ሺህ በላይ በወረርሽኙ የተያዙ ሰዎች ያሉባት አገር ስትሆን፤ በዓለም ላይ ካሉት ህሙማን ከፍተኛው ነው ተብሏል።

የሞቱ ሰዎች ቁጥርም 1,700 የሚጠጋ ሲሆን ይህ አሃዝ ግን በኮቪድ-19 በርካታ ዜጎች ከሞቱባቸው ጣሊያንና ቻይና በብዙ ርቆ የሚገኝ ነው።

ቀደም ሲል ፕሬዝዳንት ትራምፕ ፋብሪካዎች የኮሮናቫይረስን መስፋፋት ለመግታት በእራሳቸው ፍላጎት ለህክምና የሚውሉ ምርቶችን ለማምረት ሥራቸውን እየቀየሩ በመሆናቸው በሕግ መሰረት ማስገደድ አያስፈልግም ብለው ነበር።

ነገር ግን አሁን በሰጡት መግለጫ ላይ "የቫይረሱ መስፋፋት በጣም አሳሳቢ በመሆኑ በተለመደው ሁኔታ ኮንትራት ሰጥቶ የመቀበል ሂደትን ለመፈጸም የሚፈቅድ አይደለም" ብለዋል።

ፕሬዝዳንቱ ቀደም ብለውም በትዊተር ሰሌዳቸው ላይ እንዳሰፈሩት ጄነራል ሞተርስ ሊያቀርብ ቃል ገብቶት የነበረውን የመተንፈሻ መሳሪያዎች (ቬንትሌተር) ቁጥር ከፍተኛ ክፍያን በመፈለግ ከ20 ሺህ ወደ 6 ሺህ ዝቅ ማድረጉን ገልጸው የድርጅቱን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ተችተዋል።

ጄኔራል ሞተርስ ትናንት አርብ እንዳለው ከመጪው ሚያዚያ ወር ጀምሮ በየወሩ ቢያንስ 10 ሺህ ቬንትሌተሮችን ማምረት እንደሚችል አመልክቷል።

በአብዛኛው የመተንፈሻ አካላትን በተለይም ሳንባን በሚያጠቃው የኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎችን ለመርዳት የሚያገለግለው ቬንትሌተር ለህሙማኑ በጣም አስፈላጊ መሳሪያ ነው።

በአሜሪካ ውስጥ የእነዚህ መተንፈሻ መሳሪያዎች እጥረት እየተከሰተ ሲሆን የሉዊዛኒያ ግዛት ገዢ እነደተናገሩት ኒው ኦርሊንስ በጥቂት ቀናት ውስጥ ያሏትን ቬንትሌተሮች አገልግሎት ላይ አውላ ትጨርሳለች።

የአሜሪካ የህክምና ባለሙያዎች እያሉ እንዳለው ከሆነ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት 960 ሺህ ህሙማን ወደፊት የመተንፈሻ መሳሪያው ያስፈልጋቸዋል።

በወረርሸኙ ክፉኛ ከተጠቁት የአሜሪካ ግዛቶች ቀዳሚዋ የሆነችው ኒው ዮርክ 30 ሺህ ቬንትሌተሮችን ብትጠይቅም፤ ትራምፕ ግን ከፍ ያለ ግምት ነው በማለት ያን ያህል ላያስፈልግ እንደሚችምል አመልክተዋል።

ኮሮና


• ተጨማሪ ትኩስ ዜናዎች