ኮሮናቫይረስ፡ የህክምና ባለሙያዎቻቸውን ለመከላከል የሚተጉት ቱኒዚያውያን

  • 28 ማርች 2020
  • 190
የአፍና አፍንጫ መሸፈኛImage copyright Getty Images

150 ቱኒዚያውያን ራሳቸውን በፋብሪካ ውስጥ ዘግተው የፊት መሸፈኛ ጭምብል እያመረቱ ነው።

በቱኒዚያው ፋብሪካ ውስጥ የሚሰሩት እነዚህ ሠራተኞች ራሳቸውን በፋብሪካ ውስጥ በመዝጋት በቀን 50 ሺህ የፊት ጭምብል እንዲሁም ሌሎች ለሕክምና ባለሙያዎች የሚያገለግሉ የመከላከያ ቁሶችን በማምረት ላይ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል።

ሠራተኞቹ በፋብሪካ ውስጥ ራሳቸውን ነጥለው ለሕክምና ባለሙያዎች የሚያገለግሎ የተለያዩ ቁሳቁሶችን ማምረት ከጀመሩ ሳመንት ሞልቷቸዋል ተብሏል።

እነዚህ 150 ቱኒዚያውያን የፋብሪካ ሠራተኞች አብዛኛዎቹ ሴቶች ሲሆኑ በፋብሪካ ውስጥ ለአንድ ወር ያህል ዘግተው ሊቀመጡ ወስነዋል።

የኮሮናቫይረስን ለመከላከል የኢትዮጵያ ዝግጁነት ምን ይመስላል?

ሴንጋፖር አካላዊ እርቀትን የማይጠብቁ ሰዎችን በገንዘብና በእስር ልትቀጣ ነው

የፋብሪካ ሠራተኞቹ ለዚህ ውሳኔ የበቁት አገራቸው ኮሮናቫይረስን ለመዋጋት የቻለችውን እያደረገች እንደሆነ በተመለከቱ ጊዜ መሆኑን የፋብሪካው ሥራ አስኪያጅ ሐምዛ አሎኒ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ቱኒዚያውያን የፋብሪካ ሠራተኞች
Image copyright CONSOMED/AFP

በፋብሪካው ውስጥ ሠራተኛ የሆነችው ካዋላ ሬቢ ቤተሰቦቿን መናፈቋን ተናግራ ነገር ግን የባልደረቦቿ ሳቅ ጨዋታ ናፍቆቷን እንደሚያስታግስላት ትናገራለች።

"ባለቤቴና የ16 ዓመቷ ልጄ ይህንን እንዳደርግ ገፋፍተውኛል" የምትለው ሬቢ የምርት ክፍሉን እንደምትቆጣጣር ለቢቢሲ ተናግራለች።

ፋብሪካው ከዚህ በፊት የሚያመርታቸውን የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብሎችም ሆኑ ሌሎች ለሕክምና ባለሙያዎች የሚረዱ ቁሳቁሶችን ወደ ባህር ማዶ የሚልክ ቢሆንም አሁን ግን ለአገር ውስጥ ፍጆታ ብቻ እንደሚያውል ታውቋል።

የሰሜን አፍሪካዋ አገር ቱኒዚያ እስካሁን ድረስ 227 ሰዎች በኮሮናቫይረስ ሲያዙ ባለፈው ሳምንት ስድስት ህሙማን መሞታቸው ታውቋል።

ፋብሪካው ከዋና ከተማዋ ቱኒዝ በደቡባዊ አቅጣጫ ገጠራማ አካባቢ የሚገኝ ሲሆን ከፋብሪካ ሠራተኞቹ ጋር አብረው ያሉ የሕክምና ባለሙያዎች፣ የመድሃኒት ባለሙያዎችና ምግብ አብሳዮች ይገኙበታል።

ኮሮና

ለ110 ሴቶችና ለ40 ወንዶች የሚሆኑ የተለያዩ ማደሪያ ክፍሎች እንዲሁም ለአንድ ወር የሚበቃ መሰረታዊ ፍጆታ ተሟልቷል ተብሏል።

ራቢ " ለሴቶች የሚደንሱበት ወንዶች ደግሞ እግርኳስ የሚጫወቱበት የተለየ ስፍራ አዘጋጅተናል" በማለት ለሰራተኞቹ ኢንተርኔት እንዳላቸውና ሁሉም ከቤተሰቦቻቸው ጋር በቪዲዮ እንደሚያወሩ ታስረዳለች።

ፋብሪካው በሁለት ፈረቃ የሚሰራ ሲሆን የከሰአቱ ፈረቃ ላይ የተመደቡት አብዛኞቹ ወንዶች መሆናቸው ታውቋል።

አሉኒ በበኩሏ " እኛ ካልሰራን ህክምና ባለሙያዎቻችን ራሳቸውን ከቫይረሱ የሚከላከሉበት ነገር አይኖርም" በማለት ሠራተኞቹ አሁንም በወኔ እንደሚሰሩ ታስረዳለች።• ተጨማሪ ትኩስ ዜናዎች