ቴስላ ከአየር ንብረት ለውጥ ስጋት ጋር በተያያዘ ቢትኮይንን ለግብይት አይቀበልም

  • ቴስላ ከአየር ንብረት ለውጥ ስጋት ጋር በተያያዘ ቢትኮይንን ለግብይት አይቀበልም - BBC News አማርኛ

ቴስላ ከአየር ንብረት ለውጥ ስጋት ጋር በተያያዘ ቢትኮይንን ለግብይት አይቀበልም

ኤለን መስክ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

ቴስላ ከአየር ንብረት ለውጥ ስጋት ጋር በተያያዘ ቢትኮይን በመጠቀም የተሽከርካሪዎችን ሽያጭ ማገዱን ዋና ሥራ አስፈፃሚው ኤሎን መስክ በትዊተር ገፃቸው ገልፀዋል፡፡

ይህ ከተገለጸ በኋላ የቢትኮይን ዋጋ ከ 10 በመቶ በላይ ሲቀንስ የቴስላ አክሲዮኖች ዋጋም ቀንሷል፡፡

የቴስላ በመጋቢት ወር ቢትኮይን እንደሚቀበል ማስታወቁን ተከትሎ ከአንዳንድ የአካባቢ ጥበቃ ተሟጋቾች እና ባለሀብቶች ተቃውሞ ገጥሞታል፡፡

የኤሌክትሪክ መኪና አምራቹ በየካቲት ወር በ1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ከዓለም ትልቁ የዲጂታል ገንዘብ መግዛቱን ይፋ አደርጎ ነበር፡፡

ሐሙስ ግን ቀደም ሲል የነበርውን አስተያየት ማጠፉን አስታውቋል፡፡

መስክ "ለቢትኮይን ግብይት የቅሪተ አካል ነዳጅ በተለይም የድንጋይ ከሰል አጠቃቀም በፍጥነት መጨመሩ ያሳስበናል" ብለዋል፡፡

"ቢትኮይን ጥሩ ሀሳብ ነው ... ይህ ግን ተፈጥሮ ላይ ከፍተኛ ዋጋ እያስከፈለ ሊሆን አይችልም" ብለዋል ፡፡

የኤሌክትሪክ መኪና አምራቹ በእጁ የሚገኙ ቢትኮይኖችን እንደማይሸጥ እና ይበልጥ ዘላቂ ኃይልን መጠቀም ሲጀመር ለግብይቶች ሊጠቀምበት አስቧል ፡፡

የገቢያ ተንታኞች እርምጃው በቴስላ በአየር ንብረት ለውጥ እና በዘላቂነት ላይ ያተኮሩ ባለሀብቶችን ስጋት ለማሳነስ እንደተሞከረ አድርገው ይመለከቱታል፡፡

"የአካባቢ፣ ማህበራዊ እና የኮርፖሬት አስተዳደር (ኢሲጂ) ጉዳዮች አሁን ለብዙ ባለሀብቶች ትልቅ ማነቃቂያ ናቸው፡፡ ቴስላ በዘላቂ ኃይል ላይ ያተኮረ ኩባንያ በመሆኑ በተሻለ አካባቢ ለመሥራት ይፈልግ ይሆናል" ሲሉ የቡርማን ኢንቬስት ባልወደረባው ጁሊያ ሊ ለቢቢሲ የሚገልጻሉ፡፡

"ቀደም ሲል በተደጋጋገሚ እንደተደረገው ይህ ኤለን መስክ በክሪፕቶከረንሲ ገበያው ላይ ተጽዕኖ ስለማሳደራቸው ሌላው ማሳያ ነው" ሲሉ አክለው ይናገራሉ፡፡

ባለፈው ወር ቴስላ በዓመቱ የመጀመሪያዎቹ ሦስት ወሮች ያስገኘው ትርፍ 438 ሚሊዮን ዶላር ሲሆን ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል፡፡

መስክ በዓለም ላይ ካሉ የክሪፕቶከረንሲ ደጋፊዎች መካከል አንዱ ናቸው።

በቅርብ ወራቶች ትዊተር ገጻቸው መጻፋቸውን ተከትሎ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ እንደ ቀልድ የተጀመረውን ዶጅኮይንን ከዓለም አራተኛው ትልቁ ክሪፕቶከረንሲነት ለመቀየር አግዘዋል፡፡

በቢትኮይን ዙሪያ የሚነሳው የአየር ንብረት ስጋት ምንድነው?

ውስብስብ የሂሳብ እንቆቅልሾችን በመፍታት እርስ በእርስ ለመወዳደር ከፍተኛ ኃይል ያላቸው ኮምፒውተሮችን በመጠቀም ቢትኮይን ይፈጠራል፡፡

በዚህም በአብዛኛው በነዳጅ በተለይም ከድንጋይ ከሰል በሚመነጭ ኤሌክትሪክ ኃይል ላይ የተመሠረተ ሂደት ነው።

የቻይናውያን ቢትኮን የማዕድን ቆጣሪዎች የበላይነት እና ከዝቅተኛ ነዳጅ ወደ ውድ የታዳሽ የኃይል ምንጮች ለመቀየር ተነሳሽነት ማጣት በመኖሩ ቢትኮይን ላይ ለሚመነሱት ስጋቶች ፈጣን መፍትሄዎች አሉ ማለት አስቸጋሪ ነው፡፡

ቢትኮይን የሚፈጠረው 'ማይኒንግ' በሚባል ሂደት ነው። በመላው ዓለም በኔትወርክ በተሳሰሩ ኮምፒውተሮች ቁጥጥር ይደረግበታል።

በቅርብ ጊዜ በተደረገ ጥናት መሠረት ቻይና ከ75 በመቶ በላይ የሚሆነውን ቢትኮይን 'ማይን' በመናድረግ ትመራለች፡፡

ምስጠራው ምንዛሪ ካርቦን አሻራ ከቻይና አስር ትልልቅ ከተሞች እንደ አንድ ትልቅ ነው ብሏል ጥናቱ ፡፡

ለዚህም በአብዛኛው ነዳጅ በተለይም በዋነኝነት ከሰል የሚጠቀሙ ሲሆን በዝናባማው ወቅት ብቻ ወደ ታዳሽ ኃይል በመሸጋገር ይሠራሉ፡፡

የቢትኮይን ደጋፊዎች ግን ዋናው የፋይናንስ ስርዓት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሠራተኞቹ፣ የሚሠሩባቸው ባለ አየር ማቀዝቀዣ ቢሮዎች እና ኮምፒውተሮቹም በአብዛኛው ተመሳሳይ በነዳጅ የሚመረተውን ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ይጠቀማል በማለት የቢትኮይንን ምን ለየው በሚል ይጠይቃሉ ፡፡• ተጨማሪ ትኩስ ዜናዎች