ኮሮናቫይረስ፡ የፋይናንስ ዘርፉን ለመደገፍ ብሔራዊ ባንክ ተጨማሪ 15 ቢሊየን ብር ለግል ባንኮች እንዲሰጥ ተወሰነ

  • 27 ማርች 2020
  • 218
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድImage copyright PM OFFICE

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 16 በመድረሱ እና ቫይረሱ የበለጠ እንዳይዛመት ለመግታት ተጨማሪ መመሪያዎችን ይፋ አደረጉ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እነዚህን ውሳኔዎች ያሳለፉት ኮቪድ-19ን ለመከላከል ከተቋቋመው ኮሚቴ ጋር ከተወያዩ በኋላ መሆኑ ተገልጿል።

በዚህም መሰረት ከዛሬ ከሰዓት ጀምሮ ከባህር ማዶ መጥተው በተዘጋጁት ሆቴሎች ለመቆየት አቅም የሌላቸው ግለሰቦች ወደ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ እንዲዛወሩ መወሰኑ ተገልጿል።

ሴንጋፖር አካላዊ እርቀትን የማይጠብቁ ሰዎችን በገንዘብና በእስር ልትቀጣ ነው

ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን ጨምሮ፣ ትምህርት ቤቶች ለተጨማሪ ሁለት ሳምንታት ተዘግተው እንዲቆዩ መወሰኑም ተገልጿል።

ዜጎች በየትኛውም ስፍራ የማኅበራዊ ርቀት የመጠበቅን መመሪያን ተግባራዊ እንዲያደርጉ በድጋሚ ጥሪ የቀረበ ሲሆን ሁኔታው ተጨማሪ ድጋፍን የሚጠይቅ ከሆነ በሚል ሁሉም ጡረታ የወጡ እንዲሁም በትምህርት ላይ ያሉ የሕክምና ባለሙያዎች ለብሔራዊ ግዳጅ እንዲዘጋጁ ጥሪ ቀርቦላቸዋል።

የተለያየ መጠን እና ዓይነት ያላቸው መገልገያዎችን የያዙ ከ134 በላይ ተቋማት ለለይቶ መከታተያ፣ ለይቶ ማቆያ እና ሕክምና እንዲሆኑ ተለይተዋል ያለው የጠቅላይ ሚኒስትሩ መግለጫ፤ የብሔራዊ ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ የተለያዩ አካላት ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።

የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል የሚያስፈልጉ የገቢ ዕቃዎች እና ግብአቶች ከቀረጥ ነጻ እንዲገቡ የመወሰኑን የገለፀው ይህ መግለጫ ባንኮች በኮቪድ-19 ቫይረስ ለተጎዱ ደንበኞቻቸው ጊዜያዊ የብድር እፎይታ እና ተጨማሪ ብድር ለመስጠት እንዲያስችላቸው፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ተጨማሪ 15 ቢሊየን ብር ለግል ባንኮች እንዲሰጥ መወሰኑ ተገልጿል።

የውጪ ምንዛሬ የሚያስፈልጋቸው እና የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል የሚያስችሉ ዕቃዎችን እና ግብአቶችን ወደ ሀገር ውስጥ ለሚያስገቡ አስመጪዎች ባንኮች ቅድሚያ በመስጠት እንዲያስተናግዱ ይደረጋል በማለትም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለውጭ ገበያ በሚቀርብ አበባ ላይ የጣለው ዝቅተኛ የመሸጫ ዋጋ ገደብ በጊዜያዊነት እንዲነሳ መደረጉ ተነግሯል።

ኮሮና


• ተጨማሪ ትኩስ ዜናዎች