እስራኤል ወታደራዊ አመራሮችን መግደሏን ተከትሎ የሀማስ ታጣቂዎች በርካታ ሮኬቶችን ተኮሱ

  • እስራኤል ወታደራዊ አመራሮችን መግደሏን ተከትሎ የሀማስ ታጣቂዎች በርካታ ሮኬቶችን ተኮሱ - BBC News አማርኛ

እስራኤል ወታደራዊ አመራሮችን መግደሏን ተከትሎ የሀማስ ታጣቂዎች በርካታ ሮኬቶችን ተኮሱ

በጋዛ የደረሰው ጥቃት

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ,

በጋዛ የደረሰው የአየር ጥቃት

ከሰሞኑ በእስራኤልና ፍልስጥኤም መካከል ግጭት ዳግም ካገረሸ በኃላ ትላንት እስራኤል በከፈተችው የአየር ድብደባ የሃማስ ወታዳራዊ አዛዦችን ገድላለች።

በጋዛ የሚገኝ ዘርፈ ብዙ አገልግሎት የሚሰጥ ህንጻን ወደ ፍርስራሽነት ቀይራለች። ለዚህም የአጸፋ እርምጃ ሀማስ በርካታ ሮኬቶችን ወደ እስራኤል አስወንጭፏል።

ቀጣናው የገባበት ቀውስ ወደለየለት ጦርነት እንዳይሸጋገር የተባበሩት መንግስታት ድርጀት ስጋቱን ገልጾል።

ይህ ግጭት በእስራኤል ውስጥ በአይሁዶችና በእስራኤል አረቦች መካከልም የጎዳና ላይ ሁከት እንዲፈጠር ሰበብ ሆኗል። ፖለቲካዊ አመራሮች ውጥረቱን እንዲያረግቡ ተማጽኖ አቅርበዋል።

በዚህ ግጭት ምክንያት በጋዛ በትንሹ 67 በእስራኤል ደግሞ 7 ሰዎች ተገድለዋል።

ካሳምንታት ውእረት በኃላ ባለፈው ሰኞ በምስራቃዊ እየሩሳሌም ለሙሰሊሞችም ይሁን ለአይሁዶች ቅድስት ተብላ በምትቆጠር ስፍራ መነሻነት ወደ ግጭት ያመራው።

ግጭቱ በተጀመረ በሁለተኛ ቀን ደግሞ ክልስ አይሁዶችና አረቦች ተቀላቅለው በሚኖሩበት የእስራኤል አካባቢ በተፈጠረ ሁከት ምክንያት 36 የፖሊስ መኮንኖች መጎዳታቸውን የእስራኤል ፖሊስ ገልጾል ይህንንም ተከትሎ 374 ሰዎች ታስረዋል።

ትላንትና ደግሞ [ዕረቡ] በጋዛ ውስጥ የሚገኙ ታጣቂዎች ደግሞ 130 ሚሳኤሎችን መተኮሳቸውን ገልጸዋል። ይህም በጋዛ የሚገኘው አል ሻሩቅ ህንጻ በእስራኤል ለደረሰበት ጥቃት አጸፋ መሆኑንም ተናግረዋል።

በእስራኤል የአየር ድብደባ ከጥቅም ውጪ የሆነው አል ሻራርቁ በጋዛ 3ተኛው ረጅም ህንጻ ነበር።

እስራኤል በበኩሏ የሀማስን ከፍተኛ አመራሮች መግደሏን አስታውቃለች። በተጨማሪም ሚሳኤል የሚተኮስባቸውን አካባቢዎች ኢላማ አድርጋ ጥቃት መፈጸሞንም ገልጻለች። ሀማስ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦቹና "ሌሎች አመራሮች" እንደተገደሉበት አረጋግጦል።

የእስራኤል የመከላከያ ሰራዊት ሰሞኑን ጋዛ ላይ ያደረጋቸው ወታደራዊ ድብደባዎች ከ2014 በኃላ ትልቁ ነው ብሏል።• ተጨማሪ ትኩስ ዜናዎች