ትግራይ ፡ የአፍሪካ ኅብረት ልዩ መልዕክተኞች አዲስ አበባ ገቡ

  • ትግራይ ፡ የአፍሪካ ኅብረት ልዩ መልዕክተኞች አዲስ አበባ ገቡ - BBC News አማርኛ

ነገር ግን ልዑካኑ ወደ አዲስ አበባ እንደሚመጡ እንደተገለጸ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከመንግሥት ስለጉዳዩ በተሰጠ መግለጫ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ፕሬዝደንት ሲሪል ራማፎሳ የሚልኳቸውን ልዩ መልዕክተኞች በግል ተቀብለው ከማነጋገር ውጪ ድርድር እንደማይኖር አመልክቷል።

በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ መንግሥታቸው እየወሰደ ያለው እርምጃ የውስጥ ጉዳይ መሆኑን በመረዳት ጣልቃ ከመግባት እንዲቆጠቡ ማሳሰባቸው ይታወሳል።

የኢትዮጵያ መንግሥት በትግራይ ውስጥ የሚገኘው የሠሜን ዕዝ ላይ በትግራይ ኃይሎች ጥቃት ተፈጽሞ በርካታ የሠራዊቱ አባላት እንደተገደሉና በካምፑ ውስጥ የነበሩ የጦር መሣሪያዎች እንደተዘረፉ በመግለጽ ወታደራዊ እርምጃ መውሰድ ከጀመረ ከሦስት ሳምንት በላይ ሆኖታል።

ይህንንም ተከትሎ የተለያዩ አገራትና ዓለም አቀፍ ተቋማት ግጭቱ እንዲቆምና ውይይት እንዲጀመር በተደጋጋሚ ጥሪ ቢያቀርቡም የኢትዮጵያ መንግሥት በግዛቱ ውስጥ እየወሰደ ያለው "ሕግን የማስከበር እርምጃ" በመሆኑ ድርድር እንደማይኖር በተደጋጋሚ ገልጿል።

በዚህም መሰረት ተፈጸሙ ላላቸው ወንጀሎች ተጠያቂ የሆኑ የህወሓት አመራሮችን ለፍርድ ለማቅረብ ጥረት እያደረገ በመሆኑ ለድርድር እንደማይቀመጥ አሳውቋል።

በትግራይ በኩል ያሉ ባለስልጣናት ግን እራስን በራስ የማስተዳደር መብታችንን ተጠቅመን ምርጫ በማካሄዳችንና መብታችንን በማስከበራችን የፌደራል መንግሥቱ ዘመቻ ከፍቶብናል ሲሉ ይከሳሉ።

በትግራይ ክልል የተከሰተው ቀውስ አሁን ካለበት ደረጃ ላይ ከመድረሱ በፊት የህወሓት ባለስልጣንት የአፍሪካ ሕብረትና የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ጣልቃ ገብተው እንዲያሸማግሏቸው ሲጠይቁ እንደነበር ይታወሳል።

በትግራይ ውስጥ እየተካሄደ ያለው ወታደራዊ ግጭት ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያስቀመጡት ሦስት ቀናት እጅ መስጫ ቀነ ገደብ መጠናቀቁን ተከትሎ በክልሉ ዋና ከተማ ላይ የመጨረሻ ያሉት ዘመቻ መጀመሩን ዛሬ ሐሙስ ጠዋት ይፋ አድርገዋል።• ተጨማሪ ትኩስ ዜናዎች