ኮሮናቫይረስ፡ ብዙ የአየር መንገድ መዳረሻ ያላት ለንደን በሻንጋይ ተበለጠች

  • ኮሮናቫይረስ፡ ብዙ የአየር መንገድ መዳረሻ ያላት ለንደን በሻንጋይ ተበለጠች - BBC News አማርኛ
  • 54

ኮሮናቫይረስ፡ ብዙ የአየር መንገድ መዳረሻ ያላት ለንደን በሻንጋይ ተበለጠች

ኮሮናቫይረስ፡ ብዙ የአየር መንገድ መዳረሻ ያላት ለንደን በሻንጋይ ተበለጠች

ሻንጋይ ከዓለም ከተሞች ብዙ የበረራ መዳረሻ በማስመዝገብ 1ኛ ሆነች። ሻንጋይ ለንደንን በመቅደም ነው በዓለም ላይ በርካታ የአየር በረራ ግንኙነት መስመር ያላት ከተማ መሆን የቻለችው።

ሻንጋይ ለንደንን እንድትበልጥ ያስቻላት ኮሮናቫይረስ ባስከተለው ተጽእኖ ነው ተብሏል። የአየር በረራ ኢንዱስትሪው ዓለም አቀፍ ማኅበር አያታ (IATA) እንደሚለው ሎንዶን በኮቪድ ምክንያት 67% የሚሆኑ የአየር ግንኙነት መስመሮች ተሰናክለውባታል።

በዚህም የተነሳ በአየር ግንኙነት ብዛት ከለንደን ቀጥላ የነበረችው ሻንጋይ ከተማ የአንደኝነቱን ደረጃ ይዛለች። አሁን በዓለም ላይ ወደ ብዙ መዳረሻዎች የሚያደርሱ አየር መንገዶች ያሏቸው አራቱም ከተሞች የቻይና ከተሞች ሆነዋል።

አያታ እንደሚለው ለዘመናት ከተሞች የገነቡት ጠንካራ የአየር ግንኙነት ትስስር በኮቪድ ምክንያት ተቀልብሷል።“ይህ ድንገተኛ ለውጥ የሚያሳየው ባለፉት ወራት ምን ያህል ወረርሽኙ ነገሮችን እንዳመሰቃቀለ ነው” ይላሉ የዓለም አቀፉ አየር ትራንስፖርት ማኅበር (በምህጻረ ቃሉ አያታ) ቃል አቀባይ ሰባስቲያን ሚኮዝ።

ለንደን፥ ኒውዮርክና ቶክዮ በዓለም ላይ ትልልቅ የአየር ግንኙነት መስመር ያላቸው ከተሞች ሆነው ቆይተው የነበረ ሲሆን የበረራዎች መስተጓጎል እነዚህን ከተሞች ረጭ እንዲሉ አድርጓቸዋል። በአንጻሩ የአየር በረራዎች በቻይና ወደነበሩበት ሁኔታ እየተመለሱ ነው።

ጎልደን ዊክ በሚባለው የአውዳመት ወቅት 425 ሚሊዮን ሕዝብ በቻይና ከአንድ ከተማ ወደ ሌላ በአየር ተጉዟል። ቻይና የአየር መንገድ በረራዎችን መልሳ በመከፋፈት ላይ ተጠምዳለች። ከጃፓንና ሲንጋፖር ጋር በመሆን ኳረንቲን የሌለባቸው በረራዎችን የሚያስተናግድ ስምምነቶችን ለመፈረም በመነጋገር ላይ ነች።

የዓለም አቀፍ በረራ ኢንዱስትሪን የሚመራው አይታ እንደሚለው አሁን በዓለም በአየር በረራ ግንኙነት በርካታ መዳረሻ ያላቸው ሻንጋይ፣ ቤጂንግ፣ ጉዋንዡ እና ቼንግዱ ናቸው።

በዚህ ሳምንት መግቢያ በብልጽግ አገሮች ስብሰባ ላይ የቻይናው ፕሬዝዳንት ሺ ፒንግ ዓለም አንድ ወጥ የአየር መንገድ ጉዞ የማስተናበርያ ዘዴ እንዲያዘጋጅ ጠይቀዋል። እሳቸው ያመጡት ሐሳብ አንድ ወጥ የዲጂታል ኮድ ማንበብያ ያለው (QR codes) የጉዞ ሰነድ ማዘጋጀትን ነው።

በምህጻረ ቃሉ አያታ ተብሎ የሚጠራው የዓለም አቀፉ አቀፉ አየር ትራንስፖርት ማኅበር ከተሞች ወደ ሌላ ከተማ ምን ያህል መዳረሻ አላቸው የሚለውን በመገምገም የከተሞችን ደረጃ ያወጣል።

ከተሞች ወደ ተለያዩ የዓለም ከተሞች ብዙ መዳረሻ አላቸው ማለት በቱሪዝም፥ በኢንቨስትመንትና ኢኮኖሚን በማነቃቃት ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው ጠቋሚ ተደርጎ ይታሰባል።ይህ ማኅበር ባወጣው መረጃ መሰረት በአየር መንገድ በረራ ጋር በተያያዘ ብቻ በዓለም ላይ 46 ሚሊዮን ሰዎች ሥራ ችግር ውስጥ ወድቋል።

ባለፉት ሁለት ዓሥርታት በአየር መገናኘት የቻሉ ከተሞች ብዛት በእጥፍ የጨመረ ሲሆን የአየር መንገድ በረራ ዋጋ ደግሞ በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሷል።• ተጨማሪ ትኩስ ዜናዎች