በየደቂቃው በዓለም ዙሪያ በኮሮናቫይረስ የሚያዙና የሚሞቱ ሰዎች ቁጥርን የሚያሳይ ካርታ

  • 13 ማርች 2020
  • 909
ኮሮናቫይረስ ምስል

ከቻይናዋ ሁቤይ ግዛት ተነስቶ ሰው ከማይኖርበት አንታርክቲክ ውጪ ሁሉንም የዓለማችንን አህጉራትን ያዳረሰው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በአሁኑ ወቅት የምድራችን ዋነኛ የጤና ስጋት ሆኗል።

ኮቪድ-19 በመባል የሚታወቀው ይህ ወረርሽኝ የመተንፈሻ አካልን የሚያጠቃ ሲሆን፤ መጀመሪያ ትኩሳት ቀጥሎም ደረቅ ሳል ከሳምንት በኋላ ደግሞ የትንፋሽ ማጠርን ያስከትላል።

እስካሁን በቫይረሱ ከ130 ሺህ በላይ ሰዎች የተያዙ ሲሆን ከ5 ሺህ በላይ የሚሆኑ ደግሞ ህይወታቸውን አጥተዋል።