ኮሮናቫይረስ፡የህንዱ የኮቪድ ዝርያ ወደ ሰባት የአፍሪካ አገራት ተዛመተ

  • ኮሮናቫይረስ፡የህንዱ የኮቪድ ዝርያ ወደ ሰባት የአፍሪካ አገራት ተዛመተ - BBC News አማርኛ

ኮሮናቫይረስ፡የህንዱ የኮቪድ ዝርያ ወደ ሰባት የአፍሪካ አገራት ተዛመተ

የኮሮናቫይረስ ዝርያ

የፎቶው ባለመብት, AFP

ሦስት ተጨማሪ የአፍሪካ አገራት የህንድ የኮሮናቫይረስ ዝርያ እንደተዛመተባቸው የዓለም ጤና ድርጅት ባልደረባው ዶ/ር ንጎይ ንሴንጋ ለቢቢሲ ገለጹ፡፡

ሦስቱ ሃገራት አልጄሪያ፣ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና ናይጄሪያ ናቸው።

ጥናቶች ከሌሎች ዝርያዎች በበለጠ በቀላሉ እንደሚሰራጭ ያሳዩት B.1.617 የተባለው የኮቪድ ዝርያ እንደተገኘባቸው ያረጋገጡትን የአፍሪካ ሃገራት ቁጥር ወደ ሰባት አድርሶታል፡፡

በአፍሪካ የአለም ጤና ድርጅት የአፈፍሪካ የ 19-ኮቪድ -19 ም ምላሽን የሚያስተባብሩት ዶ/ር ንኔንጋ በአልጄሪያ፣ በዲሞክራቲክ ኮንጎ እና በናይጄሪያ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎችን ብዛት ወይም የጉዞ ታሪክ በተመለከተ ዝርዝር መረጃ እንደሌላቸው ተናግረዋል፡፡

በቅርቡ ወደ ህንድ ከተጓዙ ሰዎች ጋር በተያያበ አራት የአፍሪካ ሀገሮች የ B.1.617 የኮቪድ ዝርያ መኖሩን አረጋግጠዋል፡፡ እነዚህም

* ኬንያ-አምስት

* ሞሮኮ-ሁለት

* ደቡብ አፍሪካ-አራት እና

* ኡጋንዳ-አንድ ናቸው።

የዓለም የጤና ድርጅት በጥቅምት የተገኘውን የህንዱን የኮቪድ ዝርያ "በዓለም አቀፍ ደረጃ ልዩ ስጋት የፈጠረ" ብሎ ፈርጆታል፡፡

በሕንድ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ዜጎቿ ህይወታቸውን በኮቪድ የማጣታቸው እና የቫይረሱ ስርጭት መብዛት ምክንያት አዲሱ ዝርያ ስለመሆኑ እየተጠና ነው፡፡• ተጨማሪ ትኩስ ዜናዎች