በሩስያ ትምህርት ቤት በጅምላ ግድያ የተጠረጠረው ግለሰብ ክስ ተመሰረተበት

  • በሩስያ ትምህርት ቤት በጅምላ ግድያ የተጠረጠረው ግለሰብ ክስ ተመሰረተበት - BBC News አማርኛ

በሩስያ ትምህርት ቤት በጅምላ ግድያ የተጠረጠረው ግለሰብ ክስ ተመሰረተበት

ኢልናዝ ጋልያቪየቭ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

በሩስያ በአንድ ትምህርት ቤት ውስጥ ተኩስ በመክፈት ዘጠኝ ሰዎችን የገደለው ግለሰብ ድርብርብ የግድያ ክስ ተመስርቶበታል።

በደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ ክፍል በምትገኘው ካዛን ከተማ ከትላንት በስትያ [ማክሰኞ] 7 ተማሪዎች እና 2 የትምህርት ቤቱ ባለደረቦች በተከፈተባቸው የተኩስ ጥቃት ተገድለዋል።

ታዲያ ይህ ጥቃት በአውሮፓውያኑ ከ2018 በኃላ በሩሲያ በትምህርት ቤት ውስጥ የተፈጸመ የጅምላ ግድያ ሆኗል። ግድያውን እንደፈጸመ የተጠረጠረው የ19 አመቱ ኢለዚናዝ ጋሊያቪቭ ፍርድ ቤት የተወሰደ ቢሆንም ችሎቱ ላይ እንዲገኝ ግን አልተፈቀደለትም ነበር።

ጋሊያቪቭ የትምህርት ቤቱ የቀድሞ ተማሪ የነበረ ሲሆን በቅርቡ ባስመዘገበው ዝቅተኛ ውጤት ሲማርበት ከነበረው የሙያ ኮሌጅ ተሰናብቶ እንደነበር ተሰምቷል።

ጉዳዩን ከሁለት ወራት በኃላ ለማየት ፍርድ ቤት ቀጠሮ ሰጥቷል። እስከዚያው ተጠርጣሪው ሁለት ወራት በእስር እንዲቆይ ትእዛዝም አስተላልፎል።

በከባድ ወንጀሎች ላይ ምርመራ የሚያደርገው ቡድን ቢያንስ በ17 ዙር ተኩስ መክፈቱንና ፍንጂዎችንም መጠቀሙን ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል።

በዚህ ዓመት ተጠርጣሪው ቁጡና ጸበኛ ባህሪት ያሳይ እንደነበር ከዘመዶቹ ያገኘውን መረጃ መሰረት አድርጎ የምርመራ ቡድኑ ለችሎቱ የገለጸ ሲሆን ባለፈው ዓመት የአእምሮ መታወክ ገጥሞት ምርመራ ማድረጉን አብራርቷል።

በዚህ ዓመት ደግሞ ከራስ ህመም ጋር በተያያዘ ተደጋጋሚ ህክምና ማገኘቱ ተጠቁሟል።

ይህንን ጥቃት ተከትሎ ፕሬዝዳንት ቨላድሚር ፑቲን የሀገሪቱን የጦር መሳሪያ ህግ ዳግም ምለከታ እንደሚደረግበት ቃል ገብተዋል።

ሩስያ የመደበኛ ዜጎችን የጦር መሳሪያ ባለቤትነትን በተመለከት ጥብቅ ህግ አላት። የተቀመጡ መስፈርቶችን የሚያሞሉ ግለሰቦችን ለአደን፣ ራስን ለመከላከል ወይም ለስፖርት የጦር መሳሪያ መግዛት ይችላሉ።

በትምህርት ቤቱ ግድያ የተጠረጠረው ግለሰብ መሳሪያውን ሲገዛ የደህንነትና የስነልቦና ምርመራዎች እንደተደረጉለት ተሰምቷል።• ተጨማሪ ትኩስ ዜናዎች